የብጹዕ አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ የሕይወት ተጋድሎቸውን እና ድንቅ ድንቅ ስብከቶቻቸውን የያዘች የሞባይል መተግበርያ።
እጅግ አስተማሪ ሕይወት ያላቸው እውነተኛ እረኛ ናቸው። በትምህርታቸው የማይማረክ ጽሑፋቸውንም አንብቦ የማይመሰጥ የለም። እኝህ አባት ከ 40 በላይ በሆኑ ድንቅ ድንቅ መጽሐፍቶቻቸው የእኔንም ሆነ የብዙ ውጣቶችን ሕይወት አንፀዋል። በስብከታቸውና በመጽሐፍቶቻቸው የተማረኩ ብዙዎች እኝህን አባት የ 21 መቶ ክፍለ ዘመን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይላቸዋል። እኝህ አባት ስማቸው ከግብጽ አልፎ በዓለም የገነነ ነው። ሕይወታቸው እጅግ ስለሚማርክና ከቤተ ክርስቲያን አልፈው ለግብጽ ባበረከቱት አስተዋጽዖ ባረፉበት ወቅት መላው ግብጽ አዝኖ ነበር። እኝህ አባት የግብጽ ፓትሪያሪክ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ናቸው። መተግበርያ ለአገልጋዮች መልካም የሆነ ገድላቸውን ቢሰማ መልካም ነውና ታሪካቸውንና ድንቅ ድንቅ የጹሑፍ ስብከቶቻችውን በዚች አነስተኛ የስልክ መተግበርያ (Aplikasi Mudah Alih) ይዘን ቀርባለሁ።
ይህች የስልክ መተግበርያ (Aplikasi Mudah Alih) በይዘታ አንስተኛ ብትሆንም እግዚአብሔር ቢረዳን የእናንተ ጸሎት ብትደግፈኝ በየ ግዜ በራሴም እየጨመርኩኝም ሆነ ከእናንተ ከእህቶቼና ከወንድሞቼ አስተያየት እየተቀበልኩኝ እንደምለቅ ቃል እገባለሁ።
የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን! አሜን
መልካም ንባብ።