Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት


4.5.1 بواسطة Samuel Minale
08/02/2024 الإصدارات القديمة

Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላትحول

قائمة الاثيوبي Tewahedo الكنيسة الأرثوذكسية صور المقدس وMontlyYearly الأيام المقدسة

يحتوي هذا التطبيق على أكثر من 400 صورة مقدسة مختلفة للكنيسة الإثيوبية الأرثوذكسية Tewahedo القديسين الملائكة ، الآباء المقدسين ، الآباء المقدسين ، الأمهات المقدسة ، والصور المقدسة لله مع قائمة الأيام المقدسة الشهرية ، التي يتم الاحتفال بها في الكنيسة Tewahedo الأرثوذكسية وأخيرًا يحتوي التطبيق على قائمة باسم الكتاب المقدس والسحايا.

يرجى الانتباه إلى أن الصور المقدسة الموجودة في هذا التطبيق ليست الوحيدة هناك الكثير من القديسين التي لم يتم تضمينها في هذا التطبيق.

በዚህ መተግበሪያ ውስጥ ከ 400 በላይ የቅዱሳን ስዕላትን በማንኛውም ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ካለ ኢንተርኔት እንዲሰራ በመተግበሪያው ውስጥ ስእላቱ እንዲካተቱ ተደርጎዋል ፡፡

ከቅዱሳኑ በረከት ረድኤት ይደርብን

አሜን !!!

ከዚህ በታች ያለው አቡነ ገብርኤል በ 1990 ካሳተሙት "ክብረ ቅዱሳን» ከሚለው መጻሕፍ የተወሰደ ነው

የጥንቱና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተል ክርስቲያን ሁሉ ከቅዱሳት ሥዕሎች ሁለት ዐበይት ጥቅሞችን ያገኛል ይኽውም ትምህርትና ረድኤት ናቸው። ይልቁንም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረው ቃለ እግዚአብሔር (አካላዊ ቃል) በኋለኛው ዘመን ሰውን ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ከኃጢአት ብቻ በቀር ፍጹም ሰው ሆኖ በድንግልና የተወለደውና ተሰቅሎ በሞቱ ዓለሙን ማዳኑን በሥዕል ገልጾ ማቅረብ መስበክ ፤ ፤ ማስተማር ነው። በዚህም መሠረት የጌታችንን የልደቱን ታሪክ ፣ የጥምቀቱን ታሪክ ፣ የስቅለቱን ታሪክ ፣ የትንሣኤውንና የዕርገቱን ለምእመናን ማቅረብ ማለት የጌታችንን የጌታችንን መንግሥት መስበክና ማስተማር ማለት ነው ምክንያቱም ሥዕል ራሱበጉልህ የተጻፈ ጽሑፍ ማለት ነውና። ጌታችን ተወለደ ፣ ተጠመቀ ፣ ተሰቀለ ፣ ሞተ ፣ ከሙታን ተለይቶተነሣ… የሚለው የወንጌሉ ታሪክ በሥዕል ማቅረብ ማለት ታሪኩን በጉልህ ጽፎ ማቅረብ ማለት ነው።

ሐዋርያው ​​ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ተግሳጽ ሲጽፍ «የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ ፤ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር »ያለው ኢየሱስና ታሪኩን በሚገባ አውቀውትና ከልብም ተረድተውት እንደ ነበር ለመግለጽ ነው (ገላ .3 ፤ 1-2)

ስለዚህ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱሳት ሥዕሎች በመመልከትና ልብ ብሎ በማንበብ (በማስተዋል) ታሪኩን በሚገባ ማወቅና መረዳት ስለሚቻል ፤ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሥዕሎች የክርስትና ሃይማኖት አስተማሪዎችና አስረጂዎች መሆናቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው።

ሁለተኛው ጥቅም ከቅዱሳት ሥዕሎች የሚገኘው ሌላው ዐቢይ ጥቅም ደግሞ ረድኤት (ርዳታ) ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረበት በጣም ቅርብ የነበሩት የጥንት ክርስቲያኖች በጌታችን ሥዕል ፣ በቅድስት ድንግል ሥዕልና በቅዱሳን ሥዕሎች ይማፀኑ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። በዘመናችን ተቆፍረው የተገኙ የጥንት አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሶችም በሥዕላተ ቅዱሳን መማፀን ጥንታዊ ትውፊት (ሥርዓት) እንደሆነ ያመለክታሉ ታሪክን መካድ ደግሞ አያትና ቅድመ አያትን መካድ ማለት ነው። ስለ ሥዕል ክብር የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ታሪክ ምስክር ነው። የታወቀው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስዘቂሳርያ ስለ ጌታ ሥዕል አጀማመርና አመጣጥ ጽፎ ያቀረበውን ብፁእ አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘሸዋበመጽሐፋቸው ጠቅሰውታል። አኛም የጥቅሱን ፍሬ ነገር ቀጥለን ጠቅሰነዋል።

«ንጉሥ ዐብጋር በዑር (ኤዴሣ ከተማ የአገሩ ንጉሥ በመሆን ጌታችን በነበረበት ዘመን ይኖር ነበረ ፤ ስሙም (ልዑካን) ይባል ነበር። ዐብጋር ማለት በከለዳውያን ቋንቋ ቄሣር ማለት ነው። ዐብጋር በዚያ ዘመን በጠና ታሞ ተአምራት በዝና የጌታችንን ይፈውሰው ተአምራት ላከለት ፤ ጌታችንም ለጌታችን ላከለት ፤ ጌታችንም ደብዳቤውን ከመልእክተኛው እጅ ተቀብሎ ካነበበው በኋላ «ሳያየኝ ያመነኝ ዐብጋር ብፁዕ ነው» ብሎ ዐብጋርን በማመስገን በሱ ስም እንዲፈውሰው ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱን ላከለት። ነገር ግን ከጌታ ጋር ተገናኝቶ የተመለሰው የዐብጋር የዐብጋር (ዩካማ) መልእክተኛ ሠዓሊ ስለነበር ከጌታችን ጋር ሲነጋገር ፊቱን በሥዕል ነድፎ (ሥሎ) ከደብዳቤው ጋር ይዞ ተመለሰ። ከዚያም አንደ ደረሰ ከጌታ የተላከውን ደብዳቤ ለታመመው ንጉሥ አነበበለት። ሥዕሉንም አሳየው በዚያን ጊዜ ጊዜ በሽተኛው ሥዕሉንም ሥዕሉንም በዓይኑ ተመልክቶ ወዲያው ከሕመሙ እንደ ተፈወሰ ታሪኩ ያስረዳል (ያስረዳል ጎርጎርዮስ ፤ የኢ ኦ ተ ቤተ ክርስቲያንታሪክ 1974 ገጽ 119 120)።

ይኽው አውሳብዮስ ስለ ጌታችን ሥዕል የሰጠው ምስክርነት እንዲህ የሚል ነው «ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ደሙን እያንጠፈጠፈ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ጎልጎታ በሚጓዝበት ወቅት ሴቶች ሴቶች መካከል ቬሮኒካ የተባለች ደግ ሴት የራስዋን መሸፈኛ አውልቃፊቱን አንዲያድፍበት (እንዲጠርግበት ስጌታ ወረወረችለት ፤ ጌታችንም በደምና ሲመልስላት ሥዕለ ፊቱን ጠርጎ ሲመልስላት ሥዕለ ፊቱን ጠርጎ ሲመልስላት ሥዕለ ፊቱን ጠርጎ ሲመልስላት ሥዕለ ገጹ ማለት የፊቱ መልክ በሻሽዋ ላይ ታትሞ ቀረ »በማለት ከላይ የጠቀስነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ይመሰክራል።

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ደግሞ ወላዲተ አምላክ በነበረችበት ክፍለ ዘመን የነበረው ሐዋርያው ​​ቅዱስ ያዕቆብ የጌታን ታሪክ (ወንጌል) ሲጽፍ ስለ ወላዲተ አምላክም ብዙ ጽፎአል። በዚህ የያዕቆብ ወንጌል (ያዕቆብ ታሪክ) በተባለው የትውፊት መጽሐፍ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የማርያምን ሥዕል መሃሉ ተጽፎአል።

አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘቂሳርያና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እንደ መሰከሩት የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ሥዕል ፣ ለወላዲተ አምላክ አምላክ ለቅዱሳን መላእክት ሥዕሎች ሥዕሎች ከፍ ያለ ክብር እንዲደረግላቸውና እንዲቀርብላቸው ስታስተምር ኖራለች።። ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት በሚጸልዩበት ቤተ ክርስቲያንና በቤታቸው በሚገኘው በግል ጸሎት ቤታችው የጌታችንን ፣ የቅድስት ድንግል ማርያምና ​​የቅዱሳንን ሥዕሎች በግድግዳው በመስቀልና የክብር ስግደት በማቅረብሲማፀኑባቸው ኖረዋል።

በዚሁ ሁኔታ የሥዕል ክብር በጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተጠበቀ አስከ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ከቆየ በኋላ ሳይታሰብ በድንገት ከክርስቲያኖቹ መካከል ጥቂቶች ሰዎች የሥዕልን ክብር በመቃወም ተነሡ። በዚሁ ምክንያት በሮምና በቢዛንታይን ግዛቶች ከባድ ክርክርና ሁከት ተቀሰቀሰ። በዚህ ጊዜ በ 797 ዓም የምስራቅቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጉባዔ አድርገው የቅዱሳንን ሥዕሎችማክበርና መሳም (መሳለም) እንደሚገባ ለሥዕሎቹም የአክብሮት ስግደት ማቅረብ ተገቢ መሆኑን በሰፊው አትተው ወስነዋል ... ቀሪውን ከዌብሳይቱ ላይ ያንብብቡ

تحديث لأحدث إصدار 4.5.1

Last updated on 28/02/2024
Sharing Holy Picture is now added
More Holy Pictures Added
Some bugs fixed specially for android 5+ users
bugfix

معلومات أكثر ل تطبيق

احدث اصدار

4.5.1

محمل

اطياف راحلة

Android متطلبات النظام

Android 5.0+

الإبلاغ

تحديد كغير مناسب

عرض المزيد

Use APKPure App

Get Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት old version APK for Android

تحميل

Use APKPure App

Get Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት old version APK for Android

تحميل

Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት البديل

احصل على المزيد Samuel Minale

الاكتشاف